እንኳን ደህና መጡ! እፁብ ባልትና

እፁብ ባልትና በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኝ የባልትና ምርቶችን በጥራት በማዘጋጀትና በማከፋፈል ቀዳሚነትን የያዘ ድርጅት ነዉ። ድርጅታችን የሚታወቅበትን ጥራቱን የጠበቀ ምርት የማቅረብ የስራ ባህል በማዳበር ዛሬ ላለበት ደረጃ የበቃ ሲሆን፤ ወደፊትም የደንበኞቻችንን ፍላጎት የሚያረኩ ምርቶችን ለማቅረብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን።

ምን እንርዳዎ?

በአሁኑ ሰዓት ከ 65 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የባልትና ምርቶችን የምናዘጋጅ ሲሆን፤ እንጀራን ጨምሮ የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን እናዘጋጃለን። ስለምርቶቻችን የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ ምርቶቻችን የሚለዉን ቁልፍ በመጫን የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ስለድርጅታችን አመሰራረት፣ የስራ ሂደት እንዲሁም የወደፊት እቅድ ለማወቅ ከፈለጉ ስለ እፁብ የሚለዉን ቁልፍ በመጫን ማንበብ ይችላሉ። ከዚህ ባለፈ ደግሞ ድርጅታችንን በአካል፣ በስልክ ወይንም ደግሞ በኢሜይል ለማግነት ካሻዎት አድራሻችን የሚለዉን ቁልፍ በመጫን የሚፈልጉትን መልዕክት ማስተላለፍ ይችላሉ።