ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ
 በአፍሪቃ የራሰዋ የሆነ ልዩ ፊደል ያላት ብቸኛዋ ሀገር ናት፡፡
 የመጀመሪያው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም እ አ አ
በ182ዐ ተጠናቀቀ፡፡
 በኢትዮጵያ ከ8ዐ በላይ ቋንቋዎች ይነገሩባታል፡፡ 3ዐዐ የሚሆኑ
ቀበልኛ ቋንቋዎች መኖራቸውም ታውቋል፡፡
 የኢትዮጵያ የሰዓት አቈጣጠር ከእንግሊዙ ጂ.ኤም.ቲ የሰዓት
ቀመር በ3 ሰዐት ይቀድማል፡፡ የኢትዮጵያ ሰዓት አቈጣጠር
ለቀንና ለሌሊት ተለይቶ እኩል 12 ሰዓት ተመድቦለታል፡፡
 የጋሞ ሸማ ሠሪዎች /ሸማኔዎች/ የሚያመርተቸው፣ ከጥጥ
የሰሠሩ ሰርመዲዎች/ስካረፍ/፣ የወለል ምንጣፎችና በግድግደ
ላይ የሚሰቀሉ ጌጣጌጦች በዓለም በገቢያዎች ለተጠቃሢዎች
እየቀረቡ ይገኛሉ፡
 ከ85 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሽ የሚሆነው ዕድሜው
ከ2ዐ ዐመት በታች ነው፡፡
 በአፍሪቃ ረጅም ዕድሜ ይስቈጠረው ሀገራዊ የቲይትር ቤት
ከተቋቋመ 7ዐ ዓመት የሆነው የአዲስ አበባ የሀገር ፍቅር
ትያትር ቤት ነው፡፡
 ኢትዮጵያ ከአሥራ ሁለቱ የዓለም ቀዳሚ የጕዞ መዳረሻዎች
አንዷ ናት፡፡
 በኢትዮጵያ የሚገኙት ፊስቱላ ሆስፒታሎፕ ለአቅመ ሔዋን
ያልደረሱ ሴቶች በወሊድ የማኅፀን መጐዳት ሕመምን
በማከም በዓለም ላይ ብቸኞቹ የሕክምና ማዕከሎች ናቸው ፡፡
 በዓለም ብቸኛው አህዮችን በማከም ላይ የሢገኘው ሆስፒታል
 በደብረ ዘይት ከተ ይገኛል፡፡
 በአፍሪቃ በዕድሜ ረጅሙ የተፈጥሮ ፖርክ የመናገሻው ሱጳ
ፖርክ ነው፡፡
 የባሕር ዛፍ ፍሬ ከአውስትራልያ እትዮጵያ የደረሰው እ አ አ
በ1895 ነው፡፡
 በአፍሪቀ ትልቁ የመኪና አሽከርካሪዎች ትምህርት ቤት
ቃሊቲ አካባቢ የተቋቋመው ነው፡
 ትምህርት ቤቱ ውስጥ ብዙ ዘን ያገለገሉ የነባር
ተሽከርካሪዎች ሙዚየም ይገኛል፡፡
 በከተማው ማዕከል /ፒያሣ/ ወደ ሰባት የተለያዩ አካባቢዎች
የጕዞ አቅጣጫ መነሻ ያለው የኢትዮጵያ ብቸኛ ከተማ ደምቢ
ዶሎ ነው፡፡
 በኢትዮጵያ የሚበቅሉወ ሸንኮራ አገዳ፣ በዓለም ላይ ስኳር
ከሚያመረት ከማንኛወም አገር፣ በንድ ሄክታር የበለጠ
የስኳር ምርት ይሰጣል፡፡
 < ኒው ኢንተርናሽናለ ስታንዳርድ ሰሜን ሎጅ> በሚል ስም
የሚታወቀው ሆቴል፣ በአፍሪቃ ከፍተኛ በሆነ ስፍራ ላይ
የተገነባ በመሆኑ ይታወቅል፡፡ ይህ ሆቴል 3,300 ሜትር
(1ዐ,800ጫማ) ከባሕር ወለል በላይ ከፍታ አለው፡፡
 ኢትዮጵያ በቁጥር ከፍተኛ በሆኑ፣ በዓለም ቅርስነት
በተመዘገቡ ስፍራዎች ባለቤትነት ትታወቃለት፡፡
 በሰሜናዊ እትዮጵያ በበሕር ዳርና በጎንደር መካከል ባለው፣
ለም አካባቢ አውራምባ የምትባል መንደር ትገኛለች፡፡
በዚች መነር ውስጥ በሚኖሩ ወንዳችና ሴቶች መካከል
የሥራ ልዩነት የለም፡፡ ከዚህም የተኀሣ በንደርወ ውስጥ
ድህነት አይታይም፣ የመነደርዋ ሕፃናት ሁሉ ወደ ት/ቤት
ይሄዳሉ፣ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች አስፈላጊ እንክብካቤ
ይደረግላቸዋል፡

EtVisit
Please follow and like us:
0
Follow by Email
Facebook
Google+
https://etsub.com/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-2/">
Twitter