የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር

የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር

የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር

የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር ለሽያጭ የቀረበው በሐረር
ከተማ እ አ አ በ1895 ነው፡፡
 ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሕብረት አባል የሆነችው
እ አ አ በ19ዐ2 ነው፡፡
 የመጀመሪያዎቹ ሁለት መኪናዎች ኢትዮጵያ የገቡት እ አ አ
በ19ዐ2 ነው፡፡
 የመጀመሪይው ባቡር ድሬደዋ የገባው እ አ አ በ19ዐ2 ነው፡፡
 እ አ አ በ19ዐ2 የተሠራው ታላቁ ቤተ መንሥት 5ዐዐዐ
ሰዎች የሚይስተናግድ የግብር አዳራሽ አለው፡፡
 ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የተጀመረው እ አ አ
በ19ዐ5 ሲሆን፣ የመጀመሪይው ባንክ <የአቢሲኒያ ባንኩ > የሚል ሥያሜ ነበረው፡፡
 በኢትዮጵናየ የመጀመሪይው ሆቴል እ አ አ በ19ዐ7 የተከፈተው
የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ነው፡፡
 ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እ አ አ በ19ዐ8 የተከፈተው
የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነው፡፡
 እ አ አ በ191ዐ የተከፈተው የዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል
በሀገሪቱ የመጀመሪያው የመንግሠት ሆስፒታል ነው፡፡
 የመጀመሪይው የአማርኛ ቋንቋ ጋዜጣ እ አ አ በ1911
የተጀመረው <አእምሮ > ተብሎ የተሠየመው ጋዘጣ ነው፡፡
 ከጅቡቲ እስከ አዳስ አበባ የተዘረጋው የባቡር ሐዲድ
መሥመር ተሰርቶ የተጠናቀቀ እ አ አ በ1917 ነው፡፡

Please follow and like us:
0

በአንኮበር የሚገኘው የቤተመንግሥት ሙዚየም

በአንኮበር የሚገኘው የቤተመንግሥት ሙዚየም

በአንኮበር የሚገኘው የቤተመንግሥት ሙዚየም

በአንኮበር የሚገኘው የቤተመንግሥት ሙዚየም ውስጥ፣ ዳግማዊ
ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በሠርጋቸው ዕለት የለበሷቸው ሁት
በወርቅ የተለጠፋ ሙካሽ ካባዎች ይገኛሉ፡፡ የተጠለፋበት
ወርቅ ክብደት 23 ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡
 በሙዚየሙ ውስጥ በ36 ኪሎ ግራም ወርቅ የተጠለፈ
የታቦት አልባስ ይታያል፡፡ በርካታ የወርቅ ዝምዝማት
ያለባቸው ታቦታት ማንገሻ ጃንጥላዎች በሙዚየሙ ውስጥ
ይታያሉ፡፡

Please follow and like us:
0

ግማደ መስቀል

ግማደ መስቀል

ግማደ መስቀል

ክርስቶስ የተሰቀለበት <ግማደ መስቀል>በደቡብ ወሉ በግሸን
ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጠ ይገኛል፡፡
 ቤተ ክረስቲያንዋ የተሠራችው የመስቀል ቅርጽ ባለው አምባ
ላይ ነው፡፡
 ግማሽን ማርያም የምትነግሠው በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን
ነው፡

Please follow and like us:
0

ሰላም

ሰላም

ሰላም

ዕድሜዋ 3 3 ሚሚየን ዓመት የሚሆናት ፣ ፍጹም ሰው መሳይ
ዘረሰብ ቅርሰ ሕይወት፣ <ሰላም>እ አ አ በ2ዐዐዐ በቅርስ ሕይወት
ተመራማሪው በዶ/ር ዘረጨናይ ዓለምሰገድ አፋር ክልል ተገኘች፡፡
 ይህች ዘረሰብ ቅረስ ሕይወት ፣ የአውስትሮሎፒተከስ
አፋረንሲስ ዝርያ ስትሆን፣ ሌላዋ ላእለ ኮከብ ሉሲ ዕድሜዋ
3 2 ሚሊዮን ዓመት ፣ የተገኘችው እ አ አ በ1974

Please follow and like us:
0

ሴባስቶፖል

ሴባስቶፖል

ሴባስቶፖል

ሴባስቶፖል

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ፣ እ.አ.አ በ1860 ፣ ደብረ ታቦር አጠገብ በሚገኘው በጋፋት የኢንዱትሪ ስራ ይከናወን ነበር፡፡ በዚያ ስፍራ መድፎች አዳፍኔዎች ይፈበረኩ ነበር፡፡
• በጋፋት ከተፈበረኩ መሳሪያዎች መካከል ሴባስቶፖል የተሰኘው አዳፍኔ ዝነኛው ነበር፡፡ ሴባስቶፖል አዳፍኔ ክብደቱ 6.27 ቶን ሲሆ ፣ 500 የመድፍ አረሮችን እንዲተኩስ ተደርጎ የተሰራ ነበር፡፡
• የዚህ መሳሪያ በጋፋት መሰራት በመላዋ አፍሪካ ታሪክ በጊዜው አቻ የማይገኝለት ክንዋኔ ነበር ፡፡

Please follow and like us:
0

የግዕዝ ቋንቋ

የግዕዝ ቋንቋ

የግዕዝ ቋንቋ

የግዕዝ ቋንቋ

የጥንቶቹ የኢትዮጵያ የደንጊያ ላይ ፅሁፎችና የግዕዝ የፊደል ገበታ ዕድሜ ከ5ኛው ምዕተ ዓመት ቅድመ ክርስቶስ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡
• ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው የግዕዝ ቋንቋ ፤ በ6ኛው ምዕተ ዓመት ቅ.ክ በጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ተረገግጧል፡፡
• የግዕዝ ስነጽሁፍ ፣ በ4ኛው ምእተ ዓመት ድ.ክ በንጉስ ኢዛና ዘመነ መንግስት በጽኑ መሰረት ላይ የቆመ እደነበር ይነገርለታል፡፡
• የመጀመሪያው በግእዝ መዝገበ ቃላት እ.አ.አ በ1638 በሮማ ከተማ ታተመ፡፡
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስርዓቶች መፈፀሚያ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ እስከ ዘመናችን ድረስ አገልግሎቱን እነደ ቀጠለ ነው፡፡
• የኢትዮጵያ ‹ላቲን› እየተባለ ከሚጠራው የግዕዝ ቋንቋአራት ታላላቅ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ፈልቀዋል፡፡
• ‹የጠፋው መፅሐፍ ቅዱስ› እየተባለ የሚጠራው መፅሀፈ ሄኖክ፣ በግዕዝ ቋንቋ ብቻ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡

Please follow and like us:
0

ሶፍ ኡመር ዋሻ

ሶፍ ኡመር ዋሻ

ሶፍ ኡመር ዋሻ

ሶፍ ኡመር ዋሻ

በዓለም ላ እጅግ ድንቅና ውስብስብ የሆነውና 15 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሶፍ ኡመር የልበ ምድር ዋሻ የሚገኘው ባሌ ክልል ውስጥ ነው፡፡
• በአፍሪካ ግዙፉና በዓለም ላይ ታላቁ ውስብስብ የዋሻዎች መረብ የሆነው ሶፍዑመር 42 ውስጣዊ መግቢያዎች አሉት፡፡
• ሶፍ ኡመር በሙስሊሞች ዘንድ አክብሮት የሚታይ ስፍራ ነው፡፡

Please follow and like us:
0

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት

አሥራ አንዱ ድንቅና ጥንታዊ የላሊበላ (ወሎ) ውቅር አብያተ ክርስቲያን ፣ ዝናቸው በዓለም የታወቀ ነው፡፡
• የላሊበላው ቤተ መድሀኒያለም ቤተ ክስቲያን ፣ ቁመቱ 33.5 ሜትር ወርዱ 23.5 ሜትር ሲሆን ፣ በዓለም ታላቅ ውቅር ቤተክርስቲያን ነው፡፡

Please follow and like us:
0

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ገንዘቦች

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ገንዘቦች

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ገንዘቦች

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ገንዘቦች

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ንጉሰ ነገስት ኢዛና በአራተኛው ምዕተ ዓመት የክርስትና ሃይማኖት የመንግስት ሀይማኖት እንዲሆን አወጀ
• የክርስትና ሃይማኖት የመንግስት ሃይማኖት አድርጋ በመቀበል፣ ከሰሐራ በታች ካሉት የአፍሪቃ አገሮች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያ ናት ፡፡
• ንጉስ ኢዛና በአገሩ ገንዘብላይ የመስቀል ምስል እንዲቀረፅ በማድረግ በአለም የመጀመሪያው ንጉስ ነው ፡፡
• ኢትዮጵያ ለብዙ መቶ አመታት ከወርቅ በተሰሩ ገንዘቦች ትገበያይ ነበር ፡፡

Please follow and like us:
0
Follow by Email
Facebook
Google+
https://etsub.com/category/%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%9B/%E1%89%85%E1%88%AD%E1%88%B6%E1%89%BD/">
Twitter