ታላቁ ስምጥ ሸለቆ

ታላቁ ስምጥ ሸለቆ
ታላቁ ስምጥ ሸለቆ ኢትዮጵያን አቋርጦ በማለፍ፣ አገሪቱን
በብርቅዬ አእዋፋት፣ ተክሎችና እንስሳት ዝርይዎች አበልጽጓል፡፡
ጣና ሐይቅ የኢትዮጵያ ታላቁ ሐይቅ ነው፡፡ በሐይቁ ውስጥ
37 ደሴቶች ይገኛሉ፡፡ 2ዐዎቹ ደሴቶች በታሪክ፣ በእምነትና
በባህል የዳበረ ቅርስ ያላቸው አብያተ ክርስቲይንና ገዳማት
ይገኙባቸዋል፡፡
በአርባ ምንጭ አቅራቢያ የሚገኘው አባያ ሐይቅ፣ በኢትዮጵያ
ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ካሉት ሐይቆች ትልቁና ረጅሙ ሐይቅ
ነው፡፡
በአባይና በጫሞ ሐይቆች የሚረባው < ናይልፐርች>
የተሰኘው ዓሣ እስከ 1ዐዐ ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡ በእነዚሁ
ይቆች ውስጥ “ቀበኛ ‘’ የሚል ሥያሜ የተሰጠውን <ነብር ዓሣ> ማጥመድ የቻላል፡፡
የስምጥ ሸለቆው ሻላ ሐይቅ፣ 26ዐ ሜትር ጥልቀት ያለው
ሐይቅ ነው፡፡
ላንጋኖ ሐይቅ፣ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ከሚገኙት ሐይቆች ፣
አንዲ ሲሆን ፣ ዳር ዳሩ አሸዋ ያለው በመሆኑ ለዋናና በጀልባ
ለመንሸራሸር ምቹውና ብቸኛው ሐይቅ ነው፡፡
Please follow and like us: