የግዕዝ ቋንቋ
የግዕዝ ቋንቋ
የጥንቶቹ የኢትዮጵያ የደንጊያ ላይ ፅሁፎችና የግዕዝ የፊደል ገበታ ዕድሜ ከ5ኛው ምዕተ ዓመት ቅድመ ክርስቶስ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡
• ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው የግዕዝ ቋንቋ ፤ በ6ኛው ምዕተ ዓመት ቅ.ክ በጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ተረገግጧል፡፡
• የግዕዝ ስነጽሁፍ ፣ በ4ኛው ምእተ ዓመት ድ.ክ በንጉስ ኢዛና ዘመነ መንግስት በጽኑ መሰረት ላይ የቆመ እደነበር ይነገርለታል፡፡
• የመጀመሪያው በግእዝ መዝገበ ቃላት እ.አ.አ በ1638 በሮማ ከተማ ታተመ፡፡
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስርዓቶች መፈፀሚያ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ እስከ ዘመናችን ድረስ አገልግሎቱን እነደ ቀጠለ ነው፡፡
• የኢትዮጵያ ‹ላቲን› እየተባለ ከሚጠራው የግዕዝ ቋንቋአራት ታላላቅ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ፈልቀዋል፡፡
• ‹የጠፋው መፅሐፍ ቅዱስ› እየተባለ የሚጠራው መፅሀፈ ሄኖክ፣ በግዕዝ ቋንቋ ብቻ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡