የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር

የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር
የመጀመሪያ የፖስታ ቴምብር ለሽያጭ የቀረበው በሐረር
ከተማ እ አ አ በ1895 ነው፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሕብረት አባል የሆነችው
እ አ አ በ19ዐ2 ነው፡፡
የመጀመሪያዎቹ ሁለት መኪናዎች ኢትዮጵያ የገቡት እ አ አ
በ19ዐ2 ነው፡፡
የመጀመሪይው ባቡር ድሬደዋ የገባው እ አ አ በ19ዐ2 ነው፡፡
እ አ አ በ19ዐ2 የተሠራው ታላቁ ቤተ መንሥት 5ዐዐዐ
ሰዎች የሚይስተናግድ የግብር አዳራሽ አለው፡፡
ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የተጀመረው እ አ አ
በ19ዐ5 ሲሆን፣ የመጀመሪይው ባንክ <የአቢሲኒያ ባንኩ > የሚል ሥያሜ ነበረው፡፡
በኢትዮጵናየ የመጀመሪይው ሆቴል እ አ አ በ19ዐ7 የተከፈተው
የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ነው፡፡
ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እ አ አ በ19ዐ8 የተከፈተው
የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነው፡፡
እ አ አ በ191ዐ የተከፈተው የዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል
በሀገሪቱ የመጀመሪያው የመንግሠት ሆስፒታል ነው፡፡
የመጀመሪይው የአማርኛ ቋንቋ ጋዜጣ እ አ አ በ1911
የተጀመረው <አእምሮ > ተብሎ የተሠየመው ጋዘጣ ነው፡፡
ከጅቡቲ እስከ አዳስ አበባ የተዘረጋው የባቡር ሐዲድ
መሥመር ተሰርቶ የተጠናቀቀ እ አ አ በ1917 ነው፡፡
Please follow and like us: